CECA
COMMUNITY
SERVICES
ለማህበረሰብ የሚሰጡ አገልግሎቶች
CECA provides services to the community in various avenues. The following are a list of services that CECA carries for members.
1. Youth Development
The Calgary Ethiopian Community Association main focus at present is to assist the Ethiopian youth born and/or grew up in Canada to come together and establish an alliance that encourage networking and peer to peer support and development. The association wants to be attached to the youth and act as a mentor for them to be educated, responsible, law-abiding and respectable members of the city. By fostering a close relationship with the youth, the association hopes to decrease the number of youth exposed to various kinds of social problem.
2. Senior Program:
Some members are becoming senior citizens and CECA has designed a program to adapt the needs of these individuals. CECA encourages some frontline volunteers of the association to organize a coffee ceremony and invite senior citizens so that they can interact with others. By way of free membership and other initiatives, senior citizens will be encouraged to come out and stay in touch with community members.
3. Inter-community Dialogues
The Ethiopian immigrants in Canada represent different ethnic groups and nationalities within Ethiopia. Inter-community dialogues and group forums are, therefore, important to promote unity and harmony among these groups. CECA frequently organizes such dialogues, and works with local leader to promote discussion and facilitate peaceful co-existence among various groups. It also works with local government bodies to ensure that decision-making is an inclusive process that builds upon consensus among the diverse community members. Further, the association tries to use elders as mediation committee that assists in mediating group disputes. This is one of the main activities of the association that needs to be done on a continuous basis as long as new members arrive as immigrants to the City of Calgary. As part of the larger ethno-cultural community in Calgary, CECA also participates in key Afro-centric events.
4. Working with Calgary Police
As part of the Calgary Police Service Community outreach program, CECA maintains a strong tie with the Community Liaison Officer. This mutually beneficial relationship helps the Police handle culturally sensitive issues as they arise within the community.
5. Support Youth Sport and Art
CECA organizes and supports sport and art training for youth and children (both girls and boys). The program runs by volunteers and members of the association. Community-based sport and art is a program that brings people together. The sport and art programs run outdoors in summer and indoors in winter. The parents of many of these children do not have the financial capacity to join the programs offered by high-end sport and art clubs offered in the city. These community supported sport and art programs are, therefore, vital to provide the required mental and physical health and strength, as well as self-esteem enhancement and self-discipline to these children.
6. Language Classes for Children
Started in 2003 as part of the combined initiative of Calgary Public Library and the association, the CECA continues to provide occasional Amharic and English language training for children in order to support them improve their communication skills and self-expression in both languages. The program was initiated and led by CECA but often runs by volunteers. CECA rent halls and facilities, and provide teaching materials. It is often held indoors in rental facilities, community halls and schools. Non-Ethiopian Calgary families who adopted children from Ethiopia, looking to preserve their children language and cultural heritage come to use the service.
7. New comer Assistance
The CECA often assist new comers in getting settlement services, and trainings in English language, jobs searches, and other related issues. Beneficiaries include new comers from Ethiopia through our own refugee sponsorship program, co-sponsored by community members, and those who resettled from other provinces.
8. Community Outreach Program
The Community Outreach Program of CECA provides a crucial service to the community and focuses on a number of family based social issues including, financial and moral support, mitigating family violence, counseling and mediation, assistance and participation in initiatives within Calgary aimed at helping underprivileged people in Africa and particularly East Africa. It is understood that several larger organizations exist in Calgary to provide support, however, in an immigrant community, members would be seeking solutions within prior to accessing such publicly available services. CECA is routinely confronted with members going through different kinds of tragic circumstances but having no support during difficult times. Community volunteers often step-in to provide financial and moral support.
9. Family Mediation and Counselling Services
Members of the community at large are very private and routinely handle conflicts through intervention and mediation within the community. CECA provides such a forum and attempt to resolve conflicts through intervention and mediation, experience sharing, or by directing members to the appropriate service provider. Conflicts handled include spousal issues, various contractual arrangements among members (trust based issues), conflict arising from inter-religion and ethnic issues, and bridging the gap between the generation born in Canada and the first-generation immigrant parents.
10. Bereavement Counselling and Support
Loss of loved ones is handled quite differently in Ethiopian community than the western society. Repatriation of remains from Calgary, which is a common wish among the community members, alone is very expensive that is mostly handled with flash fundraising as members are unable to cover such expense. Many people routinely come to pay to their respect at each of these events which requires large organizational capacity. CECA takes a central role in leading and encouraging fund raising activities, and in general organize support groups for grieving family members.
11. Overseas Relief Effort
CECA is acutely aware of ongoing situations related to natural and man-made disasters in Ethiopia. In both issues the association supports volunteer organizers and assist them in different ways. One such annual high profile event in Calgary is the Run for Water program. CECA encourages members to participates actively in this program which aims to provide clean water to rural areas of Ethiopia.
12. Providing Support Letters
In addition to assisting members in various activities, the Association also provides members and their children with support letters when the request comes. The support letters can be to employers, public services, housing agencies, schools, and other organizations.
የካልጋሪ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማህበር በተለያዩ ጉዳዮች ለማህበረሰቡ አገልግሎት ይሰጣል። ከነዚህ ዉስጥ፣ የሚከተሉት ማህበሩ ለአባላት ከሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች ጥቂቶቹ ናቸዉ።
1. የወጣቶች ልማት ፡
የካልጋሪ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በአሁኑ ወቅት ዋና ትኩረቱ፣ በካናዳ የተወለዱ ወይም ያደጉ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን፣ አንድ ላይ በማሰባሰብ፣ ለጋራ እድገትና ለሁሉም ተሰሚነት፣ በአንድ ላይ እንዲሰሩ መርዳት ነው። ወጣቶች የተማሩ ፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ሕግን የሚያከብሩና የተከበሩ የከተማዋ አባላት ሆነው እንዲያድጉ፣ ማህበሩ ከወጣቶች ጋር ያለዉን ግንኙነት በማጠናከር፣ አስፈላዉን ምክር ይሰጣል። ማህበሩ ከወጣቱ ጋር የተቀራረበ ግንኙነት በመፍጠር ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወጣቶችን ቁጥር ለመቀነስ በተጠናከረ መልኩ ይሰራል።
2. ነባር አባላትንና አዛዉንቶችን በተመለከተ፣
ማህበሩ ከተመሰረተ የቆየ በመሆኑ፣ አንዳንድ የማህበሩ መስራች አባላት የእድሜ ባለጸጎች እየሆኑ የመጡበት ሁኔታ አለ። ከዚህ በተጨማሪ፣ ወደከተማዋ በተለያዬ መንገድ የመጡ ኢትዮጵያዉያን በእርሜ የገፉ ግለሰቦች ይኖራሉ። እነዚህ ግለሰቦች ከማህበሩና ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸዉ ግንኙነት የተጠናከረ እንዲሆን፣ ማህበሩ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በማዉጣት እየሰራ ይገኛል። ከአንዳንድ በጎ አድራጊዎች ጋር በመሆን፣ የቡና ሥነ-ስርዓት በማዘጋጀትና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት፣ በዕድሜ ከፍ ያሉ ሰዎች ከማህበሩ እንዳይርቁ የተለያዬ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፣ ወደፊትም ይደረጋል። ነጻ የአባልነትና ሌሎች ማበረታቻ ነገሮችንም በመጠቀም፣ አዛውንቶችን ወደማህበሩ ለመሳብና ከማህበረሰቡ ጋር እንዲገናኙ ያበረታታል።
3. ከተለያዩ የማህበረሰቡ አባላትና ሌሎች ማህበረሰቦች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች፣
በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የተለያዩ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን የመጡ ናቸዉ። ስለሆነም በማኅበረሰብ መካከል የሚደረጉ ውይይቶች፣ በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለማጥፋትና፣ አንድነትና ስምምነት ለማስፈን አስፈላጊ ናቸው። ማህበሩ በተለያዬ ጊዜ፣ እንዲህ ያሉ ውይይቶችን ያዘጋጃል፣ እንዲሁም በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል ሰላማዊ ትብብር እንዲኖር ከመሪዎችን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል። ማናኛዉንም ነገር አስመልክቶ የሚወሰዱ ውሳኔዎች፣ በማህበረሰብ አባላት መካከል በመግባባት ላይ የተመሠረቱ፣ ሁሉን አቀፍ መሆናቸዉን ያረጋግጣል። በተጨማሪም ማህበሩ ነባር የማህበሩ አባላትን እንደሽምግሌ በመጠቀም፣ በየጊዜዉ የሚከሰቱ ጠቦችን በሽምግልና ለምፍታት ይጥራል። አዲስ ኗሪዎች በተለያዬ ግዜ ወደ ካልጋሪ ከተማ ስለሚመጡ፣ እንደዚህ አይነት ዉይይቶች፣ ማህበሩ ከሚያኪያሄዳቸዉ ዋና ዋና ተግባራት ዉስጥ አንዱ ሆነዉ ይቀጥላሉ። የካልጋሪ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር፣ በካልጋሪ ውስጥ የተመሰረተ ነባርና ትልቅ አፍሪካዊ ድርጅት በመሆኑ፣ አፍሪካዊ ዝግጅቶች ሲኖሩም፣ በነርሱ ላይም በንቃት ይሳተፋል።
4. ከካልጋሪ ፖሊስ ጋር የሚደረጉ ስራዎችን በተመለከተ:
የካልጋሪ ፖሊስ፣ ለተለያዩ በከተማዋ ለሚኖሩ ማህበረሰቦች ለሚሰጠዉ አገልግሎት፣ ፕሮግራሙ የተሳካ ይሆን ዘንድ፣ የካልጋሪ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር (ካኢማማ)፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚሰሩ የፓሊስ አባላት ጋር በመተባበር ይሰራል። ይህ ትስስር፣ ማናቸዉንም ፣ በማህበረሰቡ ዉስጥ የሚከሰቱ ከባህል ጋር የተያያዙ ችግሮችን፣ በቀላሉ መፍትሄ እንዲገኝላቸዉ ይረዳል።
5. የወጣት ስፖርት እና ሥነ ጥበብ ድጋፍን በተመለከተ:
ካኢማማ (CECA) ለወጣት እና ለልጆች (ለሁሉም ሴት ልጆች እና ወንዶች) የስፖርት እና የስነ ጥበብ ስልጠና ያዘጋጃል፣ እንዲሁም ይደግፋል። እንደዚህ ያሉ ስልጠናዎች፣ በበጎ ፈቃደኞች እና በማኅበሩ አባላት ይሠራሉ። በማህበረሰብ ላይ የተመሠረተ ስፖርት እና ስነጥበብ ሰዎች በአንድነት እንዲቆሙ ይረዳል። የስፖርት እና የስነጥበብ ፕሮግራሞች በበጋ ወቅት ከቤት ውጭ እና በክረምት ውስጥ በቤት ውስጥ ይሰራሉ። የብዙ ልጆች ወላጆች፣ በከተማ ውስጥ ባሉ የስፖርት እና የኪነ-ጥበብ ክለቦች የሚሰጡትን መርሃግብሮች ለመቀላቀል የገንዘብ አቅም የላቸውም። ስለሆነም፣ እነዚህ በማህበረሰቡ የሚደገፉ የስፖርትና የስነጥበብ መርሃግብሮች፣ አስፈላጊውን የአእምሮ እና የአካልጤንነት እና ጥንካሬን ለመስጠት፣ እንዲሁም የልጆችን በራስ የመተማመን ግምት ለማጎልበት እጅግ አስፈላጊ በመሆናቸዉ፣ ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ፣ ማህበሩ የሚጠበቅበትን ያደርጋል።
6. የልጆች የቋንቋ ትምህርት:
ማህበሩ፣ ልጆች፣ በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች መግባባትና ራስን የመግለፅ ችሎታቸዉን እንዲያዳብሩ፣ አልፎ አልፎ የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠና እንዲሰጥ ይረዳል። ይህ በ2003 በካልጋሪ ቤተመጽሐፍትና በማህበሩ የተቀናጀ ተነሳሽነት የተጀመረ ፕሮግራም ሲሆን፣ በበጎ ፈቃደኞችና በማህበሩ አባላት የሚከናወን ነው። ማህበሩ፣ የመማሪያ አዳራሾችን ያዘጋጃል፣ የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ያቀርባል። ፕሮግራሙ እስከዛሬ (2020) ድረስ፣ በኪራይ በሚገኙ አዳራሾች፣ ተቋማትና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሲካሄድ ቆይቷል። በ2019 መጨረሻ ላይ፣ ማህበሩ የራሱ የሆነ ፋሲሊቲ ስለገዛ፣ እንደዚሀ አይነት ፕሮግራሞችን በዛ ለመስጠት እቅድ አለ። ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ፣ ግን ከኢትዮጵያ በማደጎ ልጅ በማምጣት የሚያሳድጉ በካልጋሪ የሚኖሩ ግለሰቦች፣ ልጆቻቸው፣ የወላጅ ቤተሰቦቻቸዉን ቋንቋ እና ባህል እንዳይረሱ፣ አገልግሎቱን ይጠቀሙ ዘንድ ይዘዋቸዉ ይመጣሉ።
7. ወደካልጋሪ ከተማ በቅርብ ግዜ ለሚመጡ ግለሰቦች ድጋፍ:
ማህበሩ፣ የካናዳ መንግስት በሚሰጣቸዉ የተለያዩ ፕሮግራሞች አማካኝነት፣ በየጊዜዉ ወደ ካልጋሪ የሚመጡ ግለሰቦች፣ በመቋቋሚያ አገልግሎቶች፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ በስራ ፍለጋና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ፣ ይረዳል። እነዚህ በዚህ ሁኔታ ትኩረት የሚሰጣቸዉ ግለሰቦች፣ ማህበሩ በሚሰጠዉ የስደተኞች መርጃ ፕሮግራም ወደካልጋሪ የሚመጡትንና በተለያዬ ምክንያት ከሌሎች የካናዳ ጠቅላይ ግዛቶች ወደከተማዋ የሚገቡትን ያካትታል።
8. የማኅበረሰብ ተደራሽነት ፕሮግራም:
የማህበሩ የማህበረሰብ አገልግሎት መርሃ ግብር፣ ለማህበረሰቡ አብሮ መኖር ወሳኝ ናቸዉ በተባሉ፣ በቤተሰብ ላይ በተመሰረቱ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ የገንዘብ እና የሞራል ድጋፍን ለማድረግ፣ ቤተሰብ ዉስጥ ያለን ጥቃት ለማጥፋት፣ ምክርና እና ሽምግልናን ለመስጠት፣ በኢቲዮጵያና በአፍሪካ በድህነት የሚኖሩ ግለሰቦችን ለመርዳት፣ በካልጋሪ ውስጥ በሚደረጉ እንቅሰቃሴዎች ላይ ያተኩራል። በካልጋሪ ውስጥ፣ በርካታ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል። ሆኖም ግን፣ በቅርብ ግዜ በስደት የመጡ ግለሰቦች፣ እንደዚህ ያሉ የህዝብ አገልግሎቶችን ከማግኘታቸው በፊት፣ በስደተኛዉ ማህበረሰብ ዉስጥ ያሉ መፍትሄዎችን መጠቀም ይፈልጋሉ። ማህበሩ፣ በተለያዬ ምክንያት ችግር ላይ የሚወድቁ አባላት ያጋጥሙታል። በነዚህ አጋጣሚዎች ሁሉ፣ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር፣ የገንዘብ እና የሞራል ድጋፍ በማድረግ፣ ለተቸገሩ ግለሰቦች እርዳታ ለመስጠት ይጥራል።
9. የቤተሰብና የማህበረሰብ ሽምግልና እና የምክር አገልግሎት:
በኢትዮጵያ ባህል መሰረት፣ የማህበሩ አባላት፣ በቤተሰብም ሆነ ማህበረሰብ ዉስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን፣ በግል ዉይይት፣ በሽምግልና መፍታት ይፈልጋሉ። ማህበሩ፣ እንደዚህ ዓይነት፣ ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ባህላዊ ጥረቶችን፣ ያበረታታል፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደረጋል፣ የልምድ መጋራት እንዲኖር ያግዛል። በቤተሰብና በማህበረሰብ የሚነሱ ግጭቶች፣ ከትዳር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣ በአባላት መካከል የሚደረጉ የተለያዩ የውል ስምምነቶች (እምነትን መሠረት ያደረጉ) ያማከሉ ግጭቶች፣ በሃይማኖቶችና በብሄር መካከል የሚነሱ የማያስማሙ ትርክቶች፣ እንዲሁም በካናዳ በተወለደው ትውልድና ከኢትዮጵያ በመጡ ወላጆች መካከል ባለው ክፍተት የተነሳ በቤተሰብ ዉስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን፣ የሚያጠቃልሉ ናቸዉ። በቤተሰብም ሆነ ማህበረሰብ ዉስጥ የሚከሰቱ ችግሮች በሽምግልና የማይፈቱ ከሆነ፣ የሚመለከታቸዉ ግለሰቦችም፣ ወደሚመለከተዉ የመንግስት አካል በመሄድ፣ ሀግን በተመረኮዘ መልኩ፣ በሰላም ለግጭቱ እልባት እንዲያገኙለት ይመክራል።
10. የሐዘን ማማከር እና ድጋፍ:
የሀዘንና የቀብር ስነስርአት፣ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ፣ ከምእራባዊው ማህበረሰብ ለየት ባለ ሁኔታ፣ ይታሰባል፣
ይዘከራል። በህብረተሰቡ አባላት ዘንድ የተለመደዉ ነገር፣ አንድ ሰዉ ሲሞት፣ ሬሳዉ ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ እንዲቀበር፣ መደረጉ ነዉ። ይህን ለማድረግ፣ አብዝሃኛዉ ሰዉ የገንዘብ አቅም ስሌለዉ፣ ብዙ ግዜ፣ የማህበረሰቡ አባላት አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ፣ እንዲያደርጉ ጥረት ይደረጋል። ማህበሩ፣ በእንደዚህ አይነት ወቅት፣ ከሁሉም በላይ ሀላፊነት በመዉሰድ፣ የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ፣ በመምራት እና በማበረታታት፣ ለሚመለከታቸዉ የቤተሰብ አባላት፣ ድጋፍ ለማድረግ ይሞክራል።
11. ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረግ እርዳታን በተመለተ፣
ማህበሩ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚከሰቱ ሁኔታዎችን በየወቅቱ ይከታተላል። በሚከሰቱ ጉዳዮች ማህበሩ፣ ግለሰቦች፣ የበጎ ፈቃደኞችና የእርዳታ ድርጅቶች የሚያደርጉትን መልካም ስራ ይደግፋል፣ ለመርዳትም ጥረት ያደርጋል። በየአመቱ በካልጋሪ ከሚካሄዱ እንደዚህ ያሉ የእርዳታ ማሳባሰቢያ ፕሮግራሞች ዉስጥ አንዱ፣ የ “Run for Water” ፕሮግራም ነው። ይህ ድርጅት፣ ለኢትዮጵያ የገጠር አካባቢዎች የንጹህ ውሃ ለማቅረብ በሚያደርገዉ ጥረትና በሚሰራዉ ፕሮግራም፣ አባላት በንቃት እንዲሳተፉ ማህበሩ ያበረታታል።
12. የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት፣
ማህበሩ፣ በተለያዩ ጉዳዮች አባላትን ከመርዳት በተጨማሪ፣ የማህበሩ አባላትና ወጣቶች፣ ጥያቄ በሚያቀርቡበት ግዜ፣ የድጋፍ ደብዳቤ አዘጋጅቶ ይሰጣል። የድጋፍ ደብዳቤው ለአሠሪዎች፣ ለሕዝብ አገልግሎቶች፣ ለመኖሪያ ቤት ኤጀንሲዎች፣ ለት/ቤቶች፣ ለኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ መንግስታዊ ድርጅቶች፣ እና ለሌሎች አካላት ሊሆን ይችላል።